በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህይወት እንደገና


የሪ ዲ ፋይን አባላትና ልጆች በኢትዮጵያ
የሪ ዲ ፋይን አባላትና ልጆች በኢትዮጵያ

ህይወት እንደገና (Redefine life foundation) ድርጅት ኢትዮጵያዊያን ልጆችን ለመርዳት በዋሽንግተን ዲሲ የገቢ ማሰባሰቢያ የክርክር መድረክ አካሄደ ፤ተመሳሳይ መድረኮችን በቀጣይነት እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል፡፡

በሶፊያ ገብረህይወት


ከጥቂት ሳምነታት በፊት በዚሁ በዋሺንግተን ዲሲ መዲና ህይወት እንደገና (Redifine life foundation) በተባለ ድርጅት ስር ኢትጵያውያን ወጣቶች አንድ የክርክር መድረክ አዘጋጅተው ነበር፡:

ክርክሩ የተካሄደው ‘ስደት ከጥቅሙ ጎዳቱ ያመዝናል?’ በሚል ርእስ ስር ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ ከስደተኞው ተቀባይ አገሮች ጥቅም ወይም ጎዳት አኩዋያ ብዙ የተባለለት ቢሆንም እነዚህ ወጣቶች ጥያቄ ያጤኑት ከተቀባዩ አገር ሳይሆን ከተሰዳጁ ኢትዮጵያዊ ጥቅም ወይም ጉዳት አንፃር ነበር፡፡

ስመኘው እሸቱ
ስመኘው እሸቱ


መድረኩ አገራቸውን ትተው ለመሄድ ለሚያቅዱ ኢትጵያውያን ስለውሳንያቸው ትክክለኛነት ቆም ብለው እንዲያስቡ፤ በውጭ ያሉት ወገኖቻችን ደግሞ ቀላልም ሆነ ከባድ ዋጋ ከፍለው በተገኙበት አገር በአግባቡ እንዲኖሩ የሚያሳስብ ነበር፡፡ የማበረታቻ ሽልማት ከተካሄደ በሁዋላ በገነዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም እና ክርክሩን ያዘጋጀውን ደርጅት በማስተዋወቅ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

እንደ እ.አ በ 2000 ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ትምህታቸውን በሚከታተሉ አራት ወጣቶች ነበር የተጀመረው:: ትምህርት ላይ እያሉ በባህርዳር አካባቢ የሚያዩትን የወገናቸውን ችግር ለመርዳት በአቅማቸን ማድረግ እንችላለን ከሚል በጎ ሀሳብ ነበር ተማሪዎቹ የተነሱት፡፡ ታድያ ይህ ህፃናትን ለመርዳተ በባህርዳር ከተማ የተጀመረው በጎ አድርጎት እያደገ መጥቶ በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ አባላትን አፍርተዋል፡፡

ታሪኩ ዳኘው
ታሪኩ ዳኘው

ሪ ዲፋይን ላይፍ ለድርጅቱ ማካሄጃ የሚሆነውን ገቢ የሚያገኘው በኢትዮጵያና በውጭ አገር ባሉ አባላቱ መዋጮዎች፤ ከአንዳንድ በጎ አድራጊ ግለሰቦች በሚደረግ የገንዘብ ስጦታ፤ እና አልፎ አልፍ በሚያካሂደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግሞች ነው፡፡ እንግዲህ በቅርብ በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደው የክርክር መድረክም ከነዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች አንዱ መሆኑ ነው፡፡

የክርክር መድረክ በማዘጋጅት ገንዝብ የማሰባሰቡ መንገድ ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ የሪ ዲ ፋይን ላይፍ አባላት ይህንን መንገድ የመረጡት፤ መድረኩ የምንረዳቸውን ልጆች ህይወት ለመቀየር ከማገዙ ዋነ አላማ በተጨማሪ አነጋጋሪ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የመከራከር እድል ለመፍጠር፤ በተቃራኒ ጉዳዮች ላይ በሰላማዊ መንገድ የመግባባትን ባህል ለማዳበር፤ ሰዎች እየተዝናኑ ቁምነገር የሚቀስሙበትን እድል ለመፍጠር ለመሳሰሉ ተጨማሪ አላማዎች ጭምር መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ደርጅቱ ተመሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ የክርክር መድረኮችን በቀጣይነት እንደሚያዘጋጅ አስታውቋል፡፡

የሪ ዲ ፋይን አባላት በስራ ላይ- ዋሽንግተን ዲሲ
የሪ ዲ ፋይን አባላት በስራ ላይ- ዋሽንግተን ዲሲ


ይህን ክርክር ተከትሎ የህይወት እንደገና (Redifine Life Foundation) ድርጅት አባል የሆነችውን ወ/ት ቀነኒ ዲባባ፤ በዲሲ የድርጅቱ ተወካይ እና የIT ባለሞያ እንዲሁም የድርጅቱ መስራች አባላት አንዱ ከሆነው እና በአሁኑ ጊዜ በሚቺጋን ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ትምህርቱን እየተክታተለ ካለው አብዱርራዛክ ዘይኑ (አብዲ ) ስለድርጅቱ ና ስነ ተካሄደው ክርክር በስቱዲያችን ቃለ መጠይቅ አርገንላቸው ነበር፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:23:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG