ዋሺንግተን ዲሲ —
ቀይ መስቀል ባወጣው መግለጫ ከተለቀቁት መካከል አርባ ሁለቱ በቅርቡ ዳማር ውስጥ በሚገኝ የማቆያ ማዕከል ከተፈፀምው ጥቃት የተረፉ ናቸው። ያን ጥቃት ያደረሰው ሁቲዎቹ ጋር እየተዋጋ ያለው ሳዑዲ መራሹ ጥምረት ነው ተብሎ ተወንጅሏል።
ዓለምቀፍ ቀይ መስቀል ባወጣው መግለጫ እንዳለው የእስረኞቹን ማንነት በመለየት እና በማረጋገጡ ሂደት ዕርዳታ ሰጥቷል ከተለቀቁ በኋላ የት መሄድ እንደሚፈልጉ የጤናቸውንም ይዞታ ገምግሟል። የገንዘብ ዕርዳታም አድርጎላቸዋል።
የዓለማቀፍ ቀይ መስቀል የየመን ተጠሪ ሮበርት ዚመርማን በሰጡት መግለጫ እስረኞቹ ስላሏቸው ስጋቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ግኝኙነት ይኖራቸው እንደሆን ሁሉንም በግል አነጋግረናቸዋል። ወደፊት ችግር ቢገጥማቸው ለመከታተልም አስፈላጊውን መረጃ መዝግበናል ብለዋል።
የእስረኞቹን መለቀቅ ዜና የተመድ በደስታ ተቀብሏል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ