በኢትዮጵያ የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖቶች ምእመናን፣ እንደየሥርዐተ እምነታቸው በጾም ላይ ይገኛሉ። የእርስ በርስ መተሳሰብ ጎልቶ የሚታይበት ወርኀ ጾም ታዲያ፣ ማኅበራዊ መስተጋብር የሚጠናከርበት ብቻ ሳይኾን፣ ለጤናም ከፍተኛ በረከት እንዳለው ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡
በዚኽ ጉዳይ ላይ፣ በዐዲስ አበባ የአንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ፣ የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በጋራ በታደሙበት የኢፍጣር ሥነ ሥርዐት ላይ በመታደም፣ እንዲሁም የጤና ባለሞያ አስተያየት በማካተት የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።