በአሜሪካ እና ኢራቅ ሃይሎች ጥምረት፤ በምዕራባዊ ኢራቅ በተደረገ ተልዕኮ፤ 15 የእስላማዊ መንግስት አይ ኤስ ሽብር ቡድን አባላት መገደላቸውን፤ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ሴንትኮም ትላንት አርብ አስታውቋል።
ሀሙስ ማለዳ ላይ የተፈጸመው ወረራ ዒላማ አድርጎ ያነጣጠረው የእስላማዊ መንግስት መሪዎችን ላይ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት "15 የአይ ኤስ ታጣቂዎች ሲሞቱ፤ በሲቪል ላይ ጉዳት እንደደረሰ የሚያሳይ ምንም ዓይነት ምልክት የለም” ሲል የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ዕዝ ሴትኮም በኤክስ ማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ተናግሯል።
የአይ ኤስ አባላቱ "በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ የእጅ ቦምቦች እና ፈንጂዎች እንዲሁም የአጥፍቶ ማጥፋት' ቀበቶዎች የታጠቁ ነበሩ" ያለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ልጥፉ፤ “የኢራቅ ወታደሮች ጥቃቱ የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች መቃኘታቸውን ቀጥለዋል” ሲል አስፍሯል። ይሁን እንጂ የጥቃቱን ስፍራ በደፈናው ምዕራባዊ ኢራቅ ከማለት ባለፈ የተቀመጠ ዝርዝር የለም።
ተልዕኮው የተፈፀመው ባግዳድ እና ዋሽንግተን በኢራቅ ፀረ-ጂሃዲስት ጥምር ሃይሎች መኖራቸውን አስመልክቶ ለወራት ሲነጋገሩ መቆየታቸውን ተክትሎ ነው። ይሁን እንጂ ኢራቅ ጦሯን ሙሉ በሙሉ የማስወጣት ግብ ብታስቀምጥም እስካሁን ድረስ ግን ቀነ ገደብ አልተቀመጠለትም።
የሀሙስ ዕለቱ ጥቃትም የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በሶሪያ ከአልቃይዳ ግንኙነት ያለው የታጣቂ ቡድን ከፍተኛ መሪን ከገደሉ ከአንድ ሳምንት በኋላ የተፈጸመ ነው።
መድረክ / ፎረም