ቻይና ያወጣቸው የዚሮ ኮቪድ ፖሊሲ የቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ተሰማ፡፡
ፖሊሲውን በመቃወም አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች በጋንጉዙ ከተማ ትናንት ማክሰኞ ምሽቱን ቁሳቁሶችን እያነሱ ወደ ፖሊሶች መወርወራቸው ተመልክቷል፡፡
ባለሥልጣናቱ በተቃውሞው የተሳተፉትን ተቃዋሚዎች እያሳደዱ ቢሆንም ጥብቅ የሆኑትን አንዳንዶቹን የኮቪድ ፖሊሲዎችን ማላላታቸው ተነግሯል፡፡
ከቻይናም ውጭ በኒውዮርክ እና በቶሮንቶ ካናዳ በሚገኙ የቻይና ቆንስላ ጽ/ቤቶች ፊት ለፊት መካሄዳቸው ተዘግቧል፡፡