በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብልጽግና እና ህወሓት ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር ተስማሙ


ብልጽግና እና ህወሓት ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር ተስማሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:48 0:00

ብልጽግና እና ህወሓት ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር ተስማሙ

ገዥው ፓርቲ ብልጽግና እና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/፣ ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር እንደተስማሙ፣ ህወሓት አስታወቀ።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ኘሬዝዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕርግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ በኾኑት በአቶ አደም ፋራህ የተመራው የልዑካን ቡድን፣ በመቐለ ከተማ ከህወሓት አመራሮች ጋራ ተወያይቷል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ተንታኞች፣ ፓርቲዎቹ ፖለቲካዊ ውይይት ለመጀመር የደረሱበት ውሳኔ “የዘገየ ነው” ብለዋል፡፡ ይህም ኾኖ ውይይቱ መጀመር ያለበት፣ በህወሓት እና በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት መካከል እንደኾነ፣ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት በመጥቀስ ተናግረዋል።

በዚህ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከህወሓት፣ ከብልጽግና እና ከፌደራል መንግሥት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG