No media source currently available
ብልፅግና ፓርቲ የዕውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወስኗል። የብልፅግና ፓርቲ የውጭና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ ውሳኔው የፈጠረውን ስሜት ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል። ሂደቱ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ብሄራዊ ድርጅቶች ከግንባርነት ወደ ውኅደት የተሸጋገሩበት በመሆኑ የኢህአዴግ መብቶችና ግዴታዎች ሁሉ ወደ ብልፅግና ፓርቲ ተሸጋግረዋል ብለዋል አቶ አወሉ።