የወረዳው አደጋ ስጋት ሥራ አመራር በበኩሉ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሰብአዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ከ2ሺሕ500 በላይ ዜጎች መለየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡
ለነፍስ ማዳን ሥራ ወደ ስፍራው ካቀኑት ውስጥ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህር የኾኑት ዘለቀ ዶሳ፣ በአደጋው አምስት ዘመዶቻቸውን ማጣታቸውን ጠቅሰው፣ ኹኔታው “ልብ የሚሰብርና አሠቃቂ ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዥ፣ የተከሠተውን አደጋ ለመግለጽ የሚጨንቅ መኾኑን ጠቁመው፣ ስለ ጠፋው የሰው ሕይወት ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡