በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢ-መደበኛ ጥቃቶች ለሚዲያው ፈተና ኾነዋል” - መዓዛ መሐመድ


“ኢ-መደበኛ ጥቃቶች ለሚዲያው ፈተና ኾነዋል” - መዓዛ መሐመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:31:13 0:00

የሮሃ ቴቪ ተባባሪ መሥራች እና ዋና አዘጋጅ መዓዛ መሐመድ፣ በዩቲዩብ በሚሠራጨው የብዙኃን መገናኛዋ በምታስተላልፋቸው መረጃዎች ተደጋጋሚ እስር፣ ወከባ እና ዛቻዎች ቢደርሱባትም፣ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሔደው ጦርነት ለተጎዱ ሴቶች ድምፅ መኾን በመቻሏ፣ ባለፈው ወር፣ ዩናይትድ ስቴትስ፥ በየዓመቱ አደጋን፣ ፍርሃትንና አስጨናቂ ኹኔታዎችን በቆራጥነት ተቋቁመው ሞያዊ ግዴታቸውን ለሚወጡ የአእምሮ እና የሞራል ጥቡዓን የምትሰጠውን የ“ብርቱ/ጥኑ ሴቶች”(Women of Courage) ሽልማት ተሸላሚ ኾና ነበር።

መዓዛ ሽልማቷን ለመቀበል እዚኽ ዩናይትድ ስቴትስ በመጣችበት ወቅት፣ ስመኝሽ የቆየ በአሜሪካ ድምፅ ስቱዲዮ ጋብዛ አነጋግራት ነበር። ዛሬ መዓዛን ስለ ሥራዋ እና የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛዎች አሁን ስላሉበት ኹኔታ የሰጠችውን አስተያየት፣ ዛሬ በመላው ዓለም በሚከበረው የፕሬስ ነፃነት ቀን አጋርተነዋል።

ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG