በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለኢትዮጵያ አዲስ አምባሣደር አጩ


አምባሣደር ፓትሪሽያ ኤም ሃስላች
አምባሣደር ፓትሪሽያ ኤም ሃስላችአምባሣደር ፓትሪሽያ ኤም ሃስላች
አምባሣደር ፓትሪሽያ ኤም ሃስላች

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:58 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለኢትዮጵያ አዲስ አምባሣደር አጩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በአምባሣደርነት እንደሚልኳቸው ትናንት ስማቸውን ይፋ ካደረጓቸው ስድስት አዳዲስ ተሽዋሚዎች መካከል በኢትዮጵያ መጭዋ አምባሣደር እንዲሆኑ የታሰቡት ፓትሪሽያ ኤም ሃስላች አንዷ ናቸው፡፡

አምባሣደር ሃስላች አሁን እየሠሩ ያሉት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የግጭቶችና ማረጋጋት ሥራዎች ማስተባበሪያ የሆነው አዲስ ቢሮ ዋና ምክትል ረዳት ሚኒስትር ሆነው ነው፡፡

አምባሣደር ሃስላች የአሜሪካው “መጭውን ትውልድ መመገብ - Feed the Future” የሚባለው የዓለም አቀፍ ረሃብ ማስወገጃና የምግብ ዋስትና መርኃ ግብር በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ውስጥ የዲፕሎማሲ አስተባባሪም ነበሩ፡፡

ሚስ ሃስላች በፓኪስታን የዩናይትድ ስቴትስ የምጣኔ ኃብት ቆንሲል፣ በኢንዶኔዥያና በናይጀሪያ ደግሞ ምክትል ቆንሲል ሆነው አገልግለዋል፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ግብርና ሚኒስቴር ውስጥ ይሠሩ በነበረት ጊዜም በሕንድ የአሜሪካ የአካባቢው ሃገሮች አታሼ ሆነው ሠርተዋል፡፡

እአአ ከ2004 እስከ 2007 ዓ.ም በላኦስ ሕዝባዊት ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ እና ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም ለነበሩት ዓመታትም በእሥያ-ፓሲፊክ የምጣኔ ኃብት ትብብር መድረክ /አፔክ/ የአሜሪካ አምባሣደር ሆነው አገልግለዋል፡፡

አምባሣደር ፓትሪሽያ ሃስላች በኢራቅና በአፍጋኒስታንግ ግዙፍ የሆኑ የአሜሪካ መርኃግብሮችን መርተዋል፡፡

በኦሬገን ግዛት ሌክ ኦስዌጎ የተወለዱት ሚስ ሃስላች ከዋሽንግተኑ ጎንዛጋና ከኒው ዮርኩ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ባችለርስና ማስተርስ ዲግሪዎቻቸውን አግኝተዋል፡፡

ሚስ ፓትሪሽያ ሃስላች ሽሪን እና ኪራን ኧርበርት የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆች እናት ናቸው፡፡

ዴቪድ ሺን - በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሣደር እና በዋሽንግተን ዲሲው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ረዳት ፕሮፌሰር
ዴቪድ ሺን - በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሣደር እና በዋሽንግተን ዲሲው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ረዳት ፕሮፌሰር
አምባሣደር ሃስላች “በሕይወት ዘመን አንዴ ሊገኝ የሚችል ቆንጆና ድንቅ ሃገርን ለማየት የታደሉ ሰው መሆናቸውንና ኢትዮጵያ ብዙ ሊሠሩባቸው የሚችሉ ችግሮች ያሉባት ሃገር”ም መሆኗን ለቪኦኤ በመግለፅ ስለምሥራቅ አፍሪካ ሰፊ ዕውቀት ያላቸው ቀድሞ በኢትዮጵያ አምባሣደር ሆነው ያገለገሉት በዋሽንግተን ዲሲው ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ግንኙነቶች ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን ለአዲሷ አምባሣደር መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል፡፡

የአምባሣደር ፓትሪሽያ ኤም ሃስላች ሹመት በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ከፀደቀ አዲሱን ሥራቸውን አዲስ አበባ ላይ በአዲሱ 2006 ዓ.ም መስከረም ውስጥ ይጀምራሉ፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG