4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ “ከነ ሙሉ ክብራቸውና ማዕርጋቸው ወደ አገራቸው እንዲገቡና መንበራቸው ላይ እንዲሆኑ” የሚጋብዝ፣ ከኢትዮጵያው ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የተፃፈ ደብዳቤ በማግኘታችን እውነት ስለመሆኑ ወደፕሬዚደንቱ ስንደውል፣ ፕሬዚደንት ግርማ «እውነት ነው፣ እኔ ነኝ የፃፍኩት» ብለው አረጋገጡልን።
የስልኩ ጥሪ ብዙም ጥራት ስላልነበረው እንደገና ስንደውል ደግሞ ቀደም ሲል ደብዳቤውን የፃፉት ሰዎች አሣስተዋቸው መሆኑን ጠቁመው የሻሩት መሆናቸውን ገለፁልን፡፡
ሁለቱም ውይይት ላይ ድምፃቸው አለ፤ የአዲሱ አበበን ዘገባ ያዳምጡ።