በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ባህር ላይ ሁለት መርከቦች ተጋጩ


ዩናይትድ ኪንግደም
ዩናይትድ ኪንግደም

አንድ ነዳጅ አመላላሽና አንድ የሸቀጥ አመላላሽ መርከብ በሰሜን ባህር ላይ ተጋጭተው 32 ሰዎች መጎዳታቸውንና ወደ ባህር ዳርቻ እንዲወጡ መደረጉን አንድ የእንግሊዝ ወደብ ኅላፊ አስታውቀዋል።

የተጎጂዎቹ ሁኔታን ወዲያውኑ ማወቅ እንዳልተቻለ ያመለከተው የአሶስየትድ ፕረስ ዘገባ፣ የእንግሊዝ የባህር ድንበር ኅይሎች አንድ አውሮፕላንን ጨምሮ በርካታ ነፍስ አድን ጀልባዎችንና አንድ ሄሊኮፕተር ማሰማራታቸውን አስታውቋል።

ከተጋጩት መርከቦች አንደኛው የአሜሪካንን ባንዲራ የሚያውለበልብ ሲኾን ሌላኛው ደግሞ የፖርቹጋልን ባንዲራ የሚያውለበልብ መሆኑም ታውቋል። የአሜሪካኑን ባንዲራ የሚያውለበልበውና ኬሚካልና ነዳጅ የሚያመላለሰው መርከብ ከግሪክ የተነሳ ሲሆን፣ የፖርቹጋልን ባንዲራ የሚያብለበልበው መርከብ ደግሞ ከስኮትላንድ ተነስቶ ወደ ኔዘርላንድ በማቅናት ላይ ነበር ተብሏል።

ግጭቱ እንደተከሰተ እሳት እንደተፈጠረና በርካታ ሰዎች መርከቦቹን ለቀው እንደወጡ ተመለክቷል።

በአቅራቢያው ከሚገኝ መርከብ የተቀረጸውና በቢቢሲ የተሰራጨው ቪዲዮ ከሁለቱም መርከቦች ጥቁር ጭስ ሲወጣ አሳይቷል።

የአደጋው ሥፍራ ከለንደን በስተ ሰሜን 250 ኪ.ሜ እንደሚርቅም ታውቋል

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG