በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢ ግድያ ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለፀ

ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ
ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ

ባለሥልጣናት ኢስታንቡል ቆንሲላ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የተገደለውን የሳዑዲ ዓረቢያ ስደተኛ የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢን ምርመራ እንደቀጠሉ ነው ሲሉ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ተናገሩ።

ባለሥልጣናት ኢስታንቡል ቆንሲላ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የተገደለውን የሳዑዲ ዓረቢያ ስደተኛ የጋዜጠኛ ዣማል ኻሾግዢን ምርመራ እንደቀጠሉ ነው ሲሉ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ተናገሩ።

አሜሪካዊው ከፍተኛ ዲፕሎማት ከ“ፎክስ ኒውስ” ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በግድያው እጃቸው አለበት ብላ በአመነችው 17 የሳዑዲ ሰላዮች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውሰው፣ በኻሾግዢ ላይ ያን ዘግናኝ ግድያ የፈፀሙት ግለሰቦች በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብለዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለው ግን፣ አልጋ ወራሹ ሞሃመድ ሣልማን በግድያው እጃቸው እንዳለበት የአሜሪካው የሥለላ ድርጅት /ሲአይኤ/ ቢያምንም፣ ፕሬዘዳንት ትረምፕ ለሣልማን የሰጡትን ድጋፍ በድጋሚ አስተጋብተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG