በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓምፔዎ ከሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት ጋር እየተነጋገሩ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሊየር መርኃ ግብር በተመለከተ በሃገሪቱ ዋና ከተማ ፒዮንያን የያዙትን የሁለት ቀን ውይይት የመጀመሪያውን ዛሬ አጠናቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሊየር መርኃ ግብር በተመለከተ በሃገሪቱ ዋና ከተማ ፒዮንያን የያዙትን የሁለት ቀን ውይይት የመጀመሪያውን ዛሬ አጠናቀዋል።

ሚኒስትር ፓምፔዎ ወደ ሰሜን ኮሪያ የተጓዙት የዚያች ሀገር መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለኒውክሊየር መርኃ ግብራቸው የሚያስፈልጉ መሰረት ልማቶችን መገንባታቸውን ቀጥለዋል የሚሉ የዩናይትድ ስቲትስ የደኅንነት ሪፖርቶች በወጡበት በአሁኑ ወቅት ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ወር በሲንጋፖሩ የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች ንግግር ወቅት የገባችውን ቃል ማክበሯን እንዲከታተሉ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ኃላፊነት ተሰጧቸዋል።

ትናንት ሚስተር ፖምፔዎ ከከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ገዢ ፓርቲ ባለሥልጣን እና የቀድሞ የሀሪቱ የደኅንነት ኃላፊ ከሆኑት ኪም ዮንግ ቾል ጋር ተወያይተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG