ዋሺንግተን ዲሲ —
አፍሪካ ውስጥ 47 ሃገሮችን ያቀፈው ቀጠና፣ ከፖሊዮ ነጸ መሆኑን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ትናንት ማግኘቱ ታውቋል። ፖሊዮን በማስወግድ ተግባር አዝግማ የነበርችው ናይጄሪያ፣ ከበሽታው ነፃ መሆኗ ከታወቀ በኋላ ነው፣ በቀጠና ደርጃ ምስክር ወረቀት የተሰጠው። ለሦስት ተከታታይ ዓመታት፣ ናይጄሪያ ውስጥ የፖሊዮ በሽታ እንዳልተገኘ ተዘግቧል።
በሀገርቱ በፖሊዮ ተይዘው የነበሩት ናይጄሪያውያን፣ አሁንም ተግዳሮቶች ባይለያቸውም፣ ሀገራቸው ከበሽታው ነፃ መቧሏ እንዳስደሰታቸው ገልጿል። በደስታ እያከበሩት መሆኑም ተዘግቧል።