ገዥው የፖላንድ ብሄራዊ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ‘ሕግ እና ፍትህ’ ከስምንት ዓመታት የስልጣን ዘመን በኋላ፣ በሃገሪቱ ፓርላማ የነበረውን አብላጫ መቀመጫ አጣ።
ዛሬ ማክሰኞ ይፋ የተደረገው የብሄራዊ ምርጫ ውጤት፡ ስልጣን ላይ ያለው ‘የሕግ እና የፍትህ’ ፓርቲ ሰላሳ አምስት በመቶውን የመራጭ ድምጽ ማግኘቱን አመልክቷል። በአንፃሩ ነጻ ሃሳብ አራማጁ ‘የሲቪክ ቅንጅት’ ፓርቲ ሰላሳ ነጥብ ሰባት በመቶ ድምፅ ስያገኝ፤ ማዕከላዊው ‘Third Way’ (ሶስተኛው መንገድ) የተባለው ፓርቲ 14 ነጥብ 4 እና ‘New Left’ ደግሞ 8 ነጥብ 6 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሶስቱ ፓርቲዎች በአጠቃላይ በድምሩ የመራጩን ህዝብ 53 ነጥብ 7 ድምጽ፡ እና 460 መቀመጫች ባሉት የታችኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደግሞ አብላጫውን መቀመጫ ለመያዝ መብቃታቸውን ይፋ አድርጓል።
ሶስቱ ፓርቲዎች በተናጠል ቢወዳደሩም፣ ገዥውን የሕግ እና ፍትህ ፓርቲ በምርጫ ከሥልጣን ለማስወገድ እና ፖላንድ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የነበራትን መልካም ግንኙነት ለማደስ ያላቸውን ዕቅድ አስታውቀው ነበር። የምርጫውን ውጤት ይፋ መደረግ ተከትሎም የሶስቱ ፓርቲዎች መሪዎች ጥምር መንግስት ለመመስረት ቃል ገብተዋል። ‘የሲቪክ ቅንጅት’ የተባለው ፓርቲ መሪ እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ዶናልድ ተስክ የጥምረቱ መሪ ይሆናሉ ተብሎ ታምኗል።
መድረክ / ፎረም