በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፖሃምባ ለላቀ አመራራቸው ተሸለሙ


ሄፊኬፑንዬ ፖሃምባ /የናሚቢያ ፕሬዚዳንት/
ሄፊኬፑንዬ ፖሃምባ /የናሚቢያ ፕሬዚዳንት/

በሥልጣን ዘመናቸው በአፍሪካ አህጉር የላቀ የአመራር ብልጫ ላሳዩት የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሂፊኬፑንዬ ፖሃምባ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ሽልማት ዛሬ ተሰጠ፡፡

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን
የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በሥልጣን ዘመናቸው በአፍሪካ አህጉር የላቀ የአመራር ብልጫ ላሳዩት የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሂፊኬፑንዬ ፖሃምባ የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ሽልማት ዛሬ ተሰጠ፡፡

የፕሬዚዳንት ፖሃምባ ሽልማት የአምስት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ሥጦታ ያለው ሲሆን ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ይህንን ሽልማት ሲሰጥ ባለፉት አራት ዓመታት የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ሚስተር ፖሃምባ ሕገመንግሥቱ በሚያዝዘው መሠረት ሁለት የሥልጣን ዘመን ጨርሰው እየተሰናበቱ ያሉ ሲሆን ከ1997 ዓ.ም አንስቶ ባለፉት አሥር የፖሃምባ አስተዳደር ዓመታት ውስጥ ናሚቢያ ሰላማዊና የተረጋጋ የፖለቲካ ድባብ ሰፍኖባት ቆይቷል፡፡

የሽልማት ኮሚቴው የፖሃምባን አመራር “ብልህ እና የላቀ” ሲል ጠርቶ በእርሣቸው ዘመን በናሚቢያ ዴሞክራሲ መጎልበቱን አመልክቷል፡፡

ሞ ኢብራሂም ተቋም ከሽልማቱ ጋር ባወጣው መግለጫ “የናሚቢያ ዝና በመልካም አስተዳደሯ፣ በተረጋጋ፣ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትን ጨምሮ ሁሉን አሣታፊ በሆነው ዴሞክራሲዋና ለሰብዓዊ መብቶች በሰጠችው ክብር በእጅጉ ተጠናክሯል” ብሏል፡፡

የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን ለሚስተር ፖሃምባ የወሰነውን የአምስት ሚሊዮን ዶላር ሽልማት በመጭዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ የሚከፍላቸው ሲሆን ከዚያ በኋላም በየዓመቱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ሥጦታ እንደሚልክላቸው ተገልጿል፡፡

ይህ የሞ ኢብራሂም ተቋም ሽልማት የሚሰጠው በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጦ ሥልጣን ለያዘ፤ በአመራር ዘመኑም የላቀ ውጤት ላስመዘገበና ዘመኑ ሲያበቃም ሥልጣኑን ለሚያስረክብ መሪ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG