በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠ.ሚ ኃይለማርያም መግለጫ

ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ - ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ /ፎቶ - ኤኤፍፒ/
ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሣለኝ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ - ሐምሌ 11/2006 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ /ፎቶ - ኤኤፍፒ/

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ሰሞኑን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከኤርትራ ጀምሮ የተዘረጋ መረብ አለ” አሉ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ሰሞኑን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከኤርትራ ጀምሮ የተዘረጋ መረብ አለ” አሉ፡፡

በቅርቡ ከየመን ተላልፈው የተሰጡት የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌና እርሣቸው ከሚመሩት ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የታሠሩት በሃገር ውስጥ የሚንቀሣቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች ጉዳይ ከተነሱት ፖለተካዊ ጉዳዮች መካከል ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ከዚህ በፊት በመንግሥታቸው የተሰጡ መግለጫዎችን አጠናክረዋል፡፡

ታሣሪዎቹ በሃገር ውስጥ የሚንቀሣቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች “በሕጋዊ መንገድ በተደራጁ ፓርቲዎች ውስጥ ተሸሽገው ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል” ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከኤርትራ እስከ ሶማሊያና ኬንያ የተዘረጋ የሽብር መረብ አለ፤ ዋናው ሥራችን ይህ መረብ የሚደርስበት እየደረስን መበጣጠስ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው፡፡

ለዝርዝሩ የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG