No media source currently available
የፊሊፒንስ መከላከያ ሚኒስትር ደለፊን ሎረንዛና ማራዊ በተባለችው ደቡባዊት ከተማ በአማፅያን ላይ ሲካሄድ የቆየው የአምስት ወራት ውጊያ አብቅቷል ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል። “አሁን ማራዊ ውስጥ የቀሩ አማፅያን የሉም” ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። የሀገሪቱ ወታደራዊ ሀይል ሁለት የአማጽያን መሪዎችን ከገደለ ወደ አንድ ሳምንት የሚጠጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው መከላከያው ሚኒስትር ይህን ያሉት።
አስተያየቶችን ይዩ
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ