ዋሺንግተን ዲሲ —
የፊሊፒንስ መከላከያ ሚኒስትር ደለፊን ሎረንዛና ማራዊ በተባለችው ደቡባዊት ከተማ በአማፅያን ላይ ሲካሄድ የቆየው የአምስት ወራት ውጊያ አብቅቷል ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል።
“አሁን ማራዊ ውስጥ የቀሩ አማፅያን የሉም” ሲሉ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
የሀገሪቱ ወታደራዊ ሀይል ሁለት የአማጽያን መሪዎችን ከገደለ ወደ አንድ ሳምንት የሚጠጋ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው መከላከያው ሚኒስትር ይህን ያሉት። ከተገደሉት መሪዎች አንዱ እስላማዊ መንግሥት ነኝ ለሚለው ቡድን መሪ ታማኝነቱን ገልፆ ነበር ተብሏል።
የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱተርቴ ማራዊ ከአሸባሪዎች ተፅዕኖ ነፃ ወጥታለች” ብለዋል። ወያደራዊ ባለስልጣኖች ግን ከ20 እስከ 30 የሚሆኑ የታጠቁ አማፅያን መኖራቸውን ተናግረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ