በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፔሩ 58 ኪ.ግ. ኮኬይን ተያዘ


ፖሊስ፣ በናዚ ጀርመን ባንዲራ የተጠቀለለ የአደንዛዥ እጽ ማግኘቱ ተገለጠ
ፖሊስ፣ በናዚ ጀርመን ባንዲራ የተጠቀለለ የአደንዛዥ እጽ ማግኘቱ ተገለጠ

58 ኪሎግራም የሚመዝን ኮኬይን ትናንት መያዛቸውን የፔሩ አደንዛዥ እጽ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። እሽጉ የናዚ ባንዲራ ምልክት የተደረገበትና ውደ ቤልጂየም በማቅናት ላይ እንደነበር ተነግሯል።

የአገሪቱ ፖሊስ እንዳለው ኮኬይኑ የተገኘው የላይቤሪያን ሰንደቅ ዓላማ በሚያውለበልብና የአስፋራገስ አትክልት በሚያመላልስ መርከብ ላይ ነው።

መርከቡ መጀመሪያ ኢኳዶር ላይ መልህቁን ጥሎ እንደነበርም ተጠቁሟል።

ፖሊስ በመርከቢቱ ላይ የተጫኑትን 80 የዕቃ መያዣዎች በመፈተሽ ላይ መሆኑ ታውቋል።

ከዚህ በፊት የተለያዩ ምልክቶች የተደረጉባቸው የአደንዛዥ እጽ ጥቅሎች ማግኘታቸውን የጠቀሰው ፖሊስ፣ የናዚ ጀርመን ባንዲራ ሲያገኙ ግን ለመጀመሪያ ግዜ ነው ብለዋል።

ፔሩ ከኮሎምቢያ ለጥቃ በዓለም ሁለተኛ የኮካ ቅጠል አምራች ስትሆን፣ ኮኬይን በማምረትም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

XS
SM
MD
LG