በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፔንስ ወደ ቦጎታ ኮሎምቢያ አመሩ


ምክትል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚንዳንት ማይክ ፔንስ
ምክትል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚንዳንት ማይክ ፔንስ

ምክትል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚንዳንት ማይክ ፔንስ፤ ወደ ቦጎታ ኮሎምቢያ በማምራት ላይ መሆናቸው ተገለፀ። በዩናይትድ ስቴትስ ዕውቅና ካገኙት ከቬሌዙዌላው ጊዜያዊ ፕሬዚደንትጁዋን ጉኤዶ ጋር ለመወያየትና፣ ቬኔዙዌላ ውስጥ እየተባባሰ ስለመጣው ቀውስ ለሊማው ቡድን ንግግር ለማድረግ።

ምክትል የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚንዳንት ማይክ ፔንስ፤ ወደ ቦጎታ ኮሎምቢያ በማምራት ላይ መሆናቸው ተገለፀ። በዩናይትድ ስቴትስ ዕውቅና ካገኙት ከቬሌዙዌላው ጊዜያዊ ፕሬዚደንት ጁዋን ጉኤዶ ጋር ለመወያየትና፣ ቬኔዙዌላ ውስጥ እየተባባሰ ስለመጣው ቀውስ ለሊማው ቡድን ንግግር ለማድረግ።

ምክትል ፕሬዚደንት ፔንስ እና የአካባቢው መሪዎች፣ የቬኔዙዌላው ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ሥልጣን በቶሎ ስለሚለቁበትና ለቬኔዙዌላ ተልከው ብራዚልና ኰሎምቢያ ውስጥ የተከማቹት የሰብዓዊ ዕርዳታዎች በፍጥነት ስለሚላኩበት ሁኔታ እንደሚወያዩ ታውቋል።

አንድ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል፣ ዩናይትድ ስቴትስ ሙሉውን የኢኮኖሚና የዲፕሎማቲክ ሚዛኗን በቬኔዙዌላ ላይ ለማዋል እንዳቀደች አመልክተዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስም፣ የሊማ ንግግራቸውን ከማድረጋቸው አስቀድሞ፤ ለቬኔዙዌላ የጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነት ዕውቅና ከተሰጣቸው ከጉኤዶእና ከኮሎምቢያው ፕሬዚዳንት ኢቫንዱኪው ጋር ይገናኛሉ ተብሏል።

የሊማው ቡድን ስብሰባ የሚካሄደው፣ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ ቬሌኔዙዌላ ድንበር ላይ አመፅ ከተካሄደና፣ የማዱሮስ ወታደሮች ለቬኔዙዌላ የተላከ ዕርዳታ እንዳይደርስ ዕገዳ ካደረጉ በኋላ መሆኑ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG