በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታላቁ የእግር ኳስ ንጉሥ የፔሌ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል


ብራዚላዊው የእግር ኳስ ንጉሥ ፔሌ
ብራዚላዊው የእግር ኳስ ንጉሥ ፔሌ

ለታላቁ ብራዚላዊ የእግር ኳስ ንጉሥ ለፔሌ ዛሬ በትውልድ ከተማው በሳንቶስ ጸሎተ ፍትሃት በመካሄድ ላይ ነው።

ከትናንት ጀምሮ ሀዘንተኞች ለሳንቶስ ክለብ በተጫወተበት ሳን ፓውሎ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ቪላ ቤልሚሮ ስቴዲየም ለስንብት በተቀመጠው የፔሌ አስከሬን አጠገብ እያለፉ አክብሮታቸውን እና ፍቅራቸውን በመግለጽ ተሰናብተውታል።

በሽኝት ሥነ ስርዓቱ ከተገኙት መካከል አንዱ የሰላሳ አምስት ዓመቱ እርጀንቲናዊ ጎብኚ ናሁዌል ኑኔዝ፣ "በጣም አከብረዋለሁ። ሦስት የዓለም ዋንጫ አምጥቷል። የኛም ሀገር አርጀንቲናም ሦስት የዓለም ዋንጫ ባለቤት ነች። ያሁኑን ዋንጫ እኛ ስላሸነፍን በጣም ደስ ብሎኛል። ነገር ግን ፔሌን በጣም አከብረዋለሁ። ቅርብ ቦታ ስለነበርኩ ይሄ የታሪካዊ ሰው ታሪካዊ ቀን ስለሆነ መምጣት አለብኝ ብዬ መጣሁ" ብሏል።

ሲልቪያ ዴ አብሬዉ ሱዛም በሽኝቱ ላይ ከተገኙት የፔሌ አድናቂዎች መካከል አንዷ ናቸው።

"ዛሬ ጥልቅ የሀዘን ስሜት ውስጥ የሚከት ቀን ነው። የእግር ኳሱ ንጉሡ ፔሌ በመሞቱ እናዝናለን። በዚያው ልክ ደግሞ ለከተማችን ለብራዚል ለዓለምም ጭምር ባበረከተው ስራው እንደሰታለን" ብላለች።

ታላቁ ብራዚላዊው ታላቁ የእግር ኳስ ንጉሥ ፔሌ በካንሰር ህመም ምክንያት በተወለደ በ82 ዓመቱ ያረፈው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሲሆን የጸሎተ ፍትሀት እና ሽኝት ሥነ ስርዓት ከተከናወነ በኋላ አስከሬኑ በትውልድ ከተማው በሳንቶስ ጎዳናዎች ተጉዞ ቀብሩ ይፈጸማል።

XS
SM
MD
LG