በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅሬታ እያሰሙ ነው


ሀዋሳ
ሀዋሳ

በደቡብ ክልል ለ6ተኛው ሃገራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖሊቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ሂደቱ በገዥው ፓርቲ ጫና የተሞላ፣ አስተማማኝት የጎደለው እና የተባለው ምቹ እና ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር የሌለው ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ።

ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ሁሉንም ጠቅልሎ የብልፅግና ፓርቲ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢነት የለውም ይላል የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ። ይልቁንስ ምርጫው ታዓማኒ ፥ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ከመካሰስ ይልቅ ተቀራርብን መስራት አለብን ብሏል።

ፓርቲዎቹ የተባሉትን ቅሬታቸውን ያሰሙት ዛሬ በሃዋሳ ከተማ በተደረገ በደቡብ ክልል የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአሰራር ስነ ሥርዓት ቃል ኪዳን ሰነድ ላይ በመክሩበት ወቅት መሆኑን ጠቅሶ፤ ምርጫ ቦርድ የጋር ምክር ቤት ቃል ኪዳን ስነድ እና ፓርቲዎቹ የሚደረሱባቸው ስምምነቶች ችግሩን ይፈታል ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅሬታ እያሰሙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00


XS
SM
MD
LG