በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአገራዊ ምክክር ሒደቱ የቀጠለበት ብሔራዊ ድባብ እንደሚያሳስባቸው ፓርቲዎች ገለጹ


 የአገራዊ ምክክር ሒደቱ የቀጠለበት ብሔራዊ ድባብ እንደሚያሳስባቸው ፓርቲዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:23 0:00

አገር አቀፍ ውይይት የቀጠለበት ብሔራዊ ድባብ እንደሚያሳስባቸው የገለጹት፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/ኢሕአፓ/ እና እናት ፓርቲ በሀገራዊ በምክክር ሂደቱ ለመቀጠል ቅድመ ኹኔታዎችን አስቀመጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ መላው ኢትዮጵያውያን በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበው፣ “ለሚያንገራግሩ ሰዎች ዕድሉ እንዳያመልጣችኹ” ብለዋል።

ይኹንና፣ በሒደቱ ላይ ጥያቄ እያነሡ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ የኾነው ኢሕአፓ፥ ግጭቶች እንዲቆሙ፣ የፓርቲውን ሊቀ መንበር ጨምሮ የተለያዩ እስረኞች ካልተፈቱና ሌሎች ያነሣቸው ቅድመ ኹኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ራሱን ማግለሉን ዛሬ አስታውቋል።

እናት ፓርቲ በበኩሉ፣ ያስቀመጣቸው መሰል ቅድመ ኹኔታዎች ካልተሟሉ በምክክሩ ለመሳተፍ እቸገራለኹ፤ ብሏል፡፡

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያነሧቸውን ጨምሮ ለሒደቱ መሳካት የሚያስፈልጉ ጥያቄዎችን፣ ኮሚሽኑ ለመንግሥት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡

XS
SM
MD
LG