በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በንፁሃን ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ፓርላማ ወሰነ


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

በንፁሃን ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችን አጣርቶ መረጃ እና ምክረ ሐሳብ የሚያቀርብ ልዩ ኮሚቴ እንዲቋቋም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ።

ፓርላማው ዛሬ ባካሄደው ስድስተኛው ልዩ ስብሰባ፤ በወቅታዊ የፀጥታ እና በንጹሐን ዜጎች ጉዳይ ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ዙሪያ ተወያይቶ፣ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢዎች በሲቪል ዜጎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት ያስከተሉ እና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ ውሳኔ አሳልፏል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በሰጠው መግለጫ ደግሞ በወለጋ ዞኖች እና አካባቢው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ እና በፌዴራል የጸጥታ ተቋማት እንዲመራ ጠይቋል፡፡

በኦሮምያ ክልል የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሔደ መሆኑን ጠቅሶ፣ ለዚህም መንግሥት ኦሸኔ የሚለውን እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውን አካል ተጠያቂ አድርጓል፡፡ መንግሥት እና የተወካዮች ምክር ቤትም ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ተባባሪ ናቸው ሲል ፓርቲው ከሷል፡፡

መንግሥቱ በሽብር የፈረጀውና ባለሥልጣናቱ “ሸኔ” እያሉ የሚጠሩት፤ “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” እንደሚባል የሚናገረው ታጣቂ ቡድን ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ታርቢ ደግሞ ለግድያው የመንግሥትን ታጣቂ ሚሊሺያዎችን ተጠያቂ አድርጓል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:00 0:00

XS
SM
MD
LG