የፓሪስ ኦሎምፒክ እየተቃረበ ባለበት ወቅት የክፍት የዋና ውድድሮች ሊካሄድበት የታቀደው ወንዝ የውሃ ጥራት ላይ ጥያቄ መነሳቱን ተከትሎ ወንዙ ንጹህ መሆኑን ለማሳየት የፓሪስ ከንቲባ ዛሬ ዋኝተውበታል።
ከንቲባ አን ሂዳልጎ በፓሪስ 2024 ኃላፊ ቶኒ ኢስታግንዌ እንዲሁም በፓሪስ ክልል ባለሥልታን ማርክ ጊየም በመታጀብ፣ ሴን ተብሉ በሚጠራው ወንዝ ውስጥ ዋኝተዋል።
ከንቲባዋ ከፓሪስ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እና ከዝነኛው ኖተር ዳም ካቴድራል በኩል ባለው የውንዙ ክፍል ወደ ውሃው ጠልቀዋል።
የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም አላፊ አግዳሚ የፓሪስ ነዋሪዎች በዋናው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
ከእ.አ.አ 2015 ጀምሮ፣ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት፣ 1.5 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ፣ የሴን ወንዝ ለኦሎምፒክ ውድድሩ ዝግጁ እንዲሆንና ከውድድሩ በኋላ ላሉት ረጅም ዓመታት የፓሪስ ነዋሪዎች ንፁህ ወንዝ እንዲኖራቸው ተሠርቷል።
ከአንድ መቶ ዓመታት በላይ በሴን ወንዝ መዋኘት ክልክል ነበር።
የፓሪስ ኦሎምፒክ በመጪው ሳምንት ዓርብ ይጀመራል።
መድረክ / ፎረም