በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓኪስታን የጤና ጥበቃ ሰራተኛ ተገደለች


የፓኪስታን ፖሊሶች በገለፁት መሰረት ማንኑቱ ያልታወቀ ታጣቂ አንዲት በፖልዮ ክትባት ሥራ የተሰማራች የጤና ጥበቃ ስራተኛን ተኩሶ ሲገድል ሌላዋን ደግሞ አቁስሏል።

በያዝነው ሳምንት ሲካሄድ በቆየው ብሄራዊ የፖልዮ ክትባት ዘመቻ ላይ በሚካሄደው ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ብዛት ሦስት ደርሷል።

የአሁኑ ተኩስ የተከፈተው ባሉችስታን በተባለው የደቡብ ምዕራብ ክፍለ ሀገር እንደሆነ ፖሊሶች ገልጸዋል። ከአፍጋኒስታን ጋር በሚዋሰነው በቀላሉ በማይደረስበት ወረዳ ላይ በሞተር ብስክሌት የሄዱ አጥቂዎች በፖልዮ ሰራተኞች ቡድን ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ነው ፖሊሶቹ የተናገሩ። የቆሰለችው የጤና ሰራተኛ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ፖሊሶቹ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG