በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፒፕል ቱ ፒፕል ኮንፈረንስና እውቅና የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን


ፒፕል ቱ ፒፕል የሚንከባከባቸው ወላጅ እና አሳዳጊ አልባ ህጻናት
ፒፕል ቱ ፒፕል የሚንከባከባቸው ወላጅ እና አሳዳጊ አልባ ህጻናት

በመላው ዓለም የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን በማስተባበር የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ ችግሮች ለመቅረፍና የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የተቋቋመው የፒፕል ቱ ፒፕል ድርጅት፣ 14ኛውን ዓመታዊ ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡ በድረ ገጽ ላይ በተካሄደው በዚህ የፒፕል ቱ ፒፕል ዝግጅት፣ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ጨምሮ በርካታ እንግዶችና እውቅ የጤና ባለሙያዎች ኮቪድ 19ን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ንግግር አሰምተዋል፡፡

በኮንፈረስንሱም ላይ በዋሽንግተን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋን ጨምሮ የሙያና ማህበረሰባዊ አስተዋጽኦ ያበረከቱ እውቅ ሰዎች እውቅና የተሰጣቸው መሆኑን የማህበሩን መስራችና ፕሬዚዳንት ዶ/ር እናጋው መሀሪ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

ፒፕል ቱ ፒፕል የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ፣ በሙያ በትምርህትና የእውቀት ሽግግርን በማድረግ ለመደገፍ እዚህ በዩናይትድ ስቴት የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ በኢትዮጵያም ቅርንጫፍ ከፍቶ ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ዘንድሮ የተቋቋመበትን 22ኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ በየዓመቱ የሚያካሄደው በጤና ጉዳዮች ላይ የሚተኮረው ዓለም አቀፍ ኮፈረንስ ከተጀመረ 12ኛ ዓመታዊ በዓሉን ያከበረው በወቅቱ ባለው የኮቪድ 19 ምክንያት በአካል ሳይሆን በድረ ገጽ አማካይነት ነው፡፡ በዚህ ዝግጅት ከአሜሪካና ከኢትዮጵያና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተለያዩ እንግዶችን ተሳታፊዎች ተካፍይ ሆነውበታል፡፡ በርካታ ኢትዮጵያንና የኢት ወዳጆች የሆኑትን የህክምና ባለሙያዎች የሚሳተፉበትን ይህን ድርጅት ያቋቁሙትና አሁንም በፕሬዚዳንትነት በማገልግል ላይ የሚገኙት ዶ/ር እናውጋው መሃሪ ሲሆኑ የዛሬ የኢትዮጵያውያን በአሜሪካ እንግዳችን ናቸው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የፒፕል ቱ ፒፕል ኮንፈረንስና እውቅና የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:29:15 0:00


XS
SM
MD
LG