ዋሺንግተን ዲሲ —
“ለትዳር መወለድ” በሚል ርዕስ ድርጅቱ ትናንት ባወጣው ሪፖርቱ ደቡብ ሱዳን ሴቶች ትምህርት ዕድል ከማያገኙባቸው በመላ ዓለም ካሉ እጅግ አስቸጋሪ የሚባሉ ሃገሮች አንዷ መሆኗን ጠቁሞ፤ በጋብቻ ምክንያት እጅግ የበዛ ቁጥር ያላቸው ልጃገረዶች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ እንደሚገደዱ አመልክቷል።
በቀድሞዪቱ የዩኒቲ ግዛት ከተማ ኒያል ውስጥ ለአራት ተከታታይ ዓመታት አካሂጃለሁ ያለውን ቅኝትና ጥናትና ውጤት ያስመረኮዘው ኦክስፋም፤ ከሰባ ከመቶ በላይ ልጃገረዶች የሚዳሩት ለአቅመ ሄዋን ከመድረሳቸው በፊት መሆኑን አሳውቋል።
በሃገሪቱ ውስጥ እየተካሄዱ ባሉ የርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት የተፈጠሩት ረሃብና ድኅነት ብዙ ወላጆች ለጥሎሽ ሲሉ ልጆቻቸውን በጨቅላነታቸው ለመዳር እንዲዳረጉ ያደረጓቸው መሆኑንም የኦክስፋም የደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ራንጃን ፑዲያል ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ