በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር ለጆን ኬሪ ደብዳቤ ላከ


የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር
የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር

የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር “የመብቶች ረገጣዎችን ያካሂዳል” በሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ጫና እንድታሣድር ጠይቋል፡፡

የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር
የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:18:17 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር “የመብቶች ረገጣዎችን ያካሂዳል” በሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ጫና እንድታሣድር ጠይቋል፡፡

ማኅበሩ ጥያቄውን ያቀረበው ወደኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ለተሰማው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባስገባው ደብዳቤ ነው፡፡

ዋና ፅሕፈት ቤቱ ሚኔሶታ - ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው የኦሮሞ ጥናቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ለውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ያስገቡት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በአፍሪካ ኅብረት ሃምሣኛ ዓመት በዓል አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደኢትዮጵያ ስለሚጓዙ ለኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዲያቀርቡላቸው የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች የያዘ ደብዳቤ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ጥያቄዎቹም የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ እሥረኞችን ሁሉ እንዲፈታ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞ ገበሬዎችን በኃይል እያፈናቀለ መሬታቸውን ለውጭ እና ለትግራይ ነዋይ አፍሣሾች ማከራየቱን እንዲያቆም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሬስ፣ የመናገር እና የመሰብሰብ ነፃነቶችን እንዲያከብር፣ የአሜሪካ ድምፅን ጨምሮ የራዲዮ ሥርጭቶችን ማፈኑንና ዌብሣይቶችን መጋረዱን እንዲያቆም እንዲጠይቁ የሚሉ ናቸው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዙት የዘገባ እና የሙሉው ቃለምልልስ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG