በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታንዛኒያው ድርድር እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ


የታንዛኒያው ድርድር እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:13 0:00

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል በታንዛኒያ የተጀመረው የሰላም ድርድር እንደሚቀጥል፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ሓላፊ ኃይሉ አዱኛ፣ በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋራ ያላቸውን ልዩነቶች በንግግር ለመፍታትና ድርድሩ ፍሬያማ እንዲኾን፣ መንግሥታቸው ቁርጥ አቋም እንዳለው ተናግረዋል።

የክልሉን የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታትና ኅብረተሰቡ ተረጋግቶ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ፣ የሰላም ድርድሩ አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል። ድርድሩ እንዲሳካም የተለያዩ አካላትን ትብብር ጠይቀዋል።

ባለፈው ሳምንት፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል በታንዛኒያ የተካሔደው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ድርድር፣ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ ሳይደረስ መጠናቀቁ በመንግሥት በኩል ተገልጿል። ከስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች ምን እንደኾኑና ቀጣይ ዙር ውይይትም መቼ እንደሚካሔድ፣ በሁለቱም አካላት የተገለጸ ዝርዝር የለም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG