የፍርድ ቤቶቹ በቀበሌና በወረዳዎች ደረጃ ሥራ መጀመር “የኅብረተሰቡን እንግልት አስቀርቷል፣ የፍርድ ቤቶችን ጫና ቀንሷል” ሲል የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል። መደበኛ ያልሆኑት ባህላዊ ችሎቶች አጋዥ የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጡ የክልሉ ምክር ቤት ባለፈው ዓመት ባወጣው አዋጅ ነበር።
ፍርድ ቤቶቹ ሥራ ከጀመሩባቸውና አገልግሎት እየሰጡ ካሉባቸው አካባቢዎች በኦሮምያ ልዩ ዞን ዱከም ከተማና አቃቂ ወረዳ የሚገኙ ሲሆን “ፍርድ ቤቱ የተደበቀ እና ምስክር በሌለበት ለተፈፀመ ወንጀል ሁሉ ፍትኅ የሚገኝበት ሆነው እንዳገኙት ነዋሪዎች ተናግረዋል።