በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ለተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የመንገድ ጥበት እና ብልሽት ተጠቃሽ መኾኑ ተገለጸ


በኦሮሚያ ለተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የመንገድ ጥበት እና ብልሽት ተጠቃሽ መኾኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

· 20 የዩኒቨርሲቲ መምህራን የሞቱበት ጠባቡ “ወሻ” መንገድ ማሳያ ኾኗል፤

በኦሮሚያ ክልል፣ በ2015 ዓ.ም. ያለፉት ዘጠኝ ወራት ባጋጠመ የትራፊክ አደጋ፣ ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

ለአደጋው መከሠት፥ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማነስ፣ የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ችግር እና የመንገዶች ጥበት መንሥኤዎች እንደኾኑ፣ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ደኅንነት ዘርፍ ሓላፊ ኮማንደር በላቸው ቲክ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በያዝነው ሳምንት፣ የመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችንና ሌሎች መንገደኞችን ጭኖ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው የተቋሙ ተሽከርካሪ፣ በምዕራብ አርሲ ዞን፣ ወሻ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በመገልበጡ፣ የ20 መምህራን ሕይወት ማለፉ ይታወሳል።

በሥፍራው ያለው የመንገዱ ጥበት፣ ለተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ መንሥኤ ስለ መኾኑ ተነግሯል፡፡ በችግሩ ዙሪያ፣ ከኦሮሚያ መንገዶች እና ከፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣናት መልስ ለማግኝት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

XS
SM
MD
LG