ዋሽንግተን —
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ጅማ ገነቲ ወረዳ ውስጥ መብራት ለሁለት ወር በመቋርጡ ምክንያት “የምንበላው አጣን” ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎች አቤቱታ ለማቅረብ በሰልፍ ወደ አስተዳደሩ ቢሮ ሲሄዱ ድብደባ እንደደረስባቸው የዞኑ የኦሮሞ ፌደራሊስት የዞኑ ተወካይ አቶ ደገባሱ ዋቆያ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ገደፋ ጎሹ በበኩላቸው ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ምክንያት መብራት ለአንድ ወር ተኩል መቋረጡን ገልጸው በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ ለነዋሪዎቹ አሳውቀናል ስለሰልፉና ድብደባው ግን የምናውቀው የለም ብለዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ዘገባ ያድምጡ።