ዋሽንግተን ዲሲ —
ጉደር ውስጥ አባትና ልጅ በጥይት መመታታቸውንና የአባትየው ሕይወት ማለፉን የቅርብ ጎረቤት ነኝ ያሉ ነዋሪ ገልፀውልናል። በአምቦም የሰው ሕይወት ጠፍቷል ተብሏል። በጊምቢ ሦስት ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በተጨማሪም በነቀምት፣በነጆ በመንዲና በአቅራቢያ ባሉ ከተሞች ውስጥ ውጥረ መንገሱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
መረጃውን ከመንግስት በኩል ለማጣራት የዞን ኃላፊዎች፣ የክልሉን መንግሥትና የፌደራል መንግስቱን ምላሽ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት አድርገን ነበር ስልካቸው ስለማይነሳ አልተሳካልንም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ