የክልሉ አስተዳደር፣ ትላንት እሑድ፣ በክልሉ ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ በአዲስ አበባ ምክክር አድርጓል።
በምክክሩ የተሳተፉት፣ የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሰሎሞን ታፈሰ፣ በውይይቱ ላይ ሰላምንና ጸጥታን እንዲሁም ልማትን የሚመለከቱ ጉዳዮች መነሣታቸውን ገልጸዋል።
ይኹንና፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ/ኦፌኮ/ እና ኦነግ በውይይቱ አለመሳተፋቸውን አክለው ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከትያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡