በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሪጂን አፍሪካ - 2015 አዲስ አበባ ላይ ተከፈተ


ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና አምባሣደር ፓትሪሺያ ሃስላክ የዕደ-ጥበብ ምርቶችን ሲጎበኙ
ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና አምባሣደር ፓትሪሺያ ሃስላክ የዕደ-ጥበብ ምርቶችን ሲጎበኙ

አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ የተከፈተው “ኦሪጂን አፍሪካ - 2015” የሚባል የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅና አልባሣት ኢንደስትሪ ኤግዚቢሽን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚከፍት ተገልጿል፡፡

አምባሣደር ፓትሪሺያ ሃስላክ የዕደ-ጥበብ ምርቶችን ሲጎበኙ
አምባሣደር ፓትሪሺያ ሃስላክ የዕደ-ጥበብ ምርቶችን ሲጎበኙ

ኦሪጂን አፍሪካ - 2015 አዲስ አበባ ላይ ተከፈተ /ርዝመት፡-5ደ34ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ የተከፈተው “ኦሪጂን አፍሪካ - 2015” የሚባል የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅና አልባሣት ኢንደስትሪ ኤግዚቢሽን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚከፍት ተገልጿል፡፡

የፊታችን የካቲት ሥራ ይጀምራል የተባለው የአዲስ አበባ - ጂቡቲ የባቡር አገልግሎት ለሃገሪቱ ኢንዱስትሪዎች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሊያበረክት እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

የሃገሪቱ ሁለተኛው የዕድገትና የለውጥ ዕቅድ የኃይል፣ የመንገድ፣ የሃዲድና የቴሌኮምዩኒኬሽን አውታሮችን ይበልጥ በማስፋፋት ላይ እንደሚያተኩር የገለፁት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሐዋሣ ከተማ ውስጥ እየተገነባ ያለውና የፊታችን የካቲት እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው የኢንዱስትሪ መናኸሪያ ለመግባት እስከአሁን አርባ የሚሆኑ ዓለምአቀፍ ታዋቂነት ያላቸው ኩባንያዎች የየራሣቸውን ሥፍራ ለመያዝ መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር ፓትሪሺያ ሃስላክም የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያና በሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች ላይ ያለውን የመዋዕለ-ነዋይ ፍሰት የአመለካከት መዛባት ለመቀየር የሚደረጉትን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ ለምጣኔ-ኃብት ዕድገት ቁልፍ የሆነውን የሃገር ውስጥና የውጭ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት ለመሣብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

“እኛ በአፍሪካ እናምናለን” ብለዋል አምባሣደር ሃስላክ፡፡

ለዝርዝሩ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ለተጨማሪ ከሥር ያለውን ማገናኛ ይዘው ይከተሉና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲን ዌብሣይት ይጎብኙ

http://photos.state.gov/libraries/ethiopia/956093/PDF%20Files/PR%20no%2041%20U_S_%20Supports%20Trade%20and%20Investment%20in%20East%20Africa-%20Origin%20Africa%202015%20_Amharic_.pdf

XS
SM
MD
LG