በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በአዲስ አበባ


ONLF
ONLF

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

በግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ሄርሞጌ የተመራው እና ፫ አባላትን ያለው ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ሲደርስ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሣሁን ጎፌ አቀባበል አድርገዋል።

ወደ ሀገር የገባውን ልዑክ የመሩት አቶ አዳኒ አብዱልቃድር ሄርሞጌ፥ ግንባሩ ወደ ሀገር ቤት ለመግባት የወሰነው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጥሪን ተከትሎ መሆኑን አስታውቀዋል።

እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ታስቦ በዚህ ፍጥነት ወደ ሀገር መግባታቸውንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ኦብነግ ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ አቁም ማወጁን የተናገሩት አቶ አዳኒ፥ ይህም በቀጠናው ምንም አይነት የጥይት ድምፅ እንዳይሰማ ስለሚፈልግ እና ክልሉን ለማረጋጋት መሆኑንም አስታውቀዋል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ መብትን ለመጠበቅ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል ያሉት ቃል አቀባዩ፥ ኦብነግም ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ሀገር ገብቶ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑን ገልፀዋል።

ለግንባሩ ልኡክ አቀባበል ያደረጉት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ካሣሁን ጎፌ በበኩላቸው፥ መንግሣት ባደረገው ጥሪ መሰረት በርካታ የፖለቲካ ሀይሎች ወደ ሀገር ቤት መግባታቸውን ጠቅሰዋል።

መንግሥትም እነዚህ የፖለቲካ ኃይሎችን ለሚያደናቅፉ አሰራሮች መፍትኄ በመስጠት እና አማራጮችን በማስፋት ራሳቸውን ለምርጫ እንዲያዘጋጁ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የተናጠል የተኩስ አቁም ማወጁ ይታወሳል።

ኦብነግ የተናጥል የተኩስ ቁም ውሳኔ ላይ የደረሰውም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ እንደሆነም ግንባሩ በመግለጫው አስታውቋል።

የኢትዮያ መንግሣትም የተጀመረው የሰላም ሂደት ግቡን እስኪመታ በግንባሩ ላይ ላይ የሚካሄዱ ወታደራዊ ይሁን ሌሎች ዕርምጃዎችን እንዲያቂምም ጥሪውን አቅርቧል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 28 2010 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) የሽብርተኝነት ፍረጃ ማንሳቱ ይታወሳል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2003 ዓ/ም ነበር ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት ፯ እንዲሁም ከሀገር ውጪ አልቃይዳና አልሸባብን ጨምሮ አሸባሪ ድርጅቶች ብሎ የፈረጀው ራድዮ ፋና እንደዘገበው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG