በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የYahoo! አካውንት ተደፍሯል!


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

እርስዎ የYahoo! አካውንት አለዎት? መረጃዎችም የግል ገመናዎ ተሰርቀው ሊሆን ይችላል፤ ችላ አይበሉ፡፡ ከአንጋፋዎቹና ከግዙፎቹ የነፃ ኢሜል አግልግሎት ሰጭዎች አንዱ የሆነው ‘ያሁ’ ውስጥ ከተያዙ ተገልጋዮች መካከል የአንድ ቢሊዮኑ የግል መረጃዎች ብዙው ተሰርቋል፡፡

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ይህ ግዙፍ ዘርፍ የተፈጠረው በነሃሴ 2013 ዓ.ም. (እአአ) ሲሆን የእገሌ መንግሥት አይባልበት እንጂ በሴራና በሰርጎ ገብ የዘረፈ ዘመቻው ውስጥ የመንግሥት እጅ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

የተለያዩ የዜና ምንጮች የነኀሴ 2013ቱን ጊዜ ይጠቀሙ እንጂ ያሁ ራሱ ለተገልጋዮቹ በላከው ማስታወቂያ የገለፀው የመረጃ ካዝናው የተደፈረው በ2014ዓ.ም. መጨረሻ ላይ መሆኑን ነው፡፡(ልክ የዛሬ ሁለት ዓመት መሆኑ ነው፡፡)

የተሠረቁት መረጃዎች ስሞችን፣ የኢሜል አድራሻዎችን፣ የስልክ ቁጥሮችን፣ የልደት ቀንና ዓመተ- ምህረትን፣ የማለፊያ የምስጢር ቁልፎችን (ፓስወርዶችን) እንዲሁም የምሥጢር ጥያቄና መልሶችን መሆኑ ያሁ አሳውቋል፡፡

ያሁን ግዙፉ የስልክ አገልግሎት ኩባንያ ቨራይዘን ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ክፍያ ሊገዛ እየተዋዋለ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ያንን የሽያጭ ሃሣብና ንግግር እየከለሰና እያጠናው መሆኑን ተናግሯል፡፡

ቨራይዘን የያሁን መረጃ የሚፈልገው ለማስታወቂያ ሥርጭት ንግድ ሲሆን ምናልባት የተሰረቁት መረጃዎች የተዝረከረኩ ከሆኑ ግዥው ቨራይዘንን እምብዛም ላይስበው ይችል ይሆናል እየተባለ ነው፡፡

ለማንኛውም ቨራይዘን 'አልገዛም' ብሎ በይፋ የተናገረው ነገር የለም፤ 'ግድ የለም እገዛዋለሁ'ም አላለም፡፡

የሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ግን ከያሁ ጋር ሆነው ጉዳዩን እያጣሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለማንኛውም ግን እርስዎ ያየሁ አካውንት ካለዎት ቁልፍ የሚሏቸውን መረጃዎች ጠበቅ አድርገው ይቆልፉ፤ ወይም ያሽሹ - ፓስወርዶችዎንም ዛሬ ነገ ሳይሉ ይቀይሩ፡፡ ሌባ እንደይጨፍርብዎ! “ተሰርቋል”

ተብሎ ዛሬ የተነገረው ያሁን የወጋውና ሌሎችንም ነክቶ ሊሆን የሚችለው ጦር ጫፍ ብቻ ልትሆን ትችላለች... የብዙዎች ሥጋትና ጥርጣሬ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG