የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በቅርቡ በጋምቤላ ከተማ በንጹሃን ዜጎችላይ ተፈፀመ ያለው ጥቃት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል።
በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን እየተዘዋወረ ያለውበመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እንደተፈፀመ የሚያሳየው ግድያ እንዲጣራ እና ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።
የጋምቤላ ክልል መንግሥት ክልሉን ከታጣቂዎች ለመከላከል ተካሄደ ባሉት ጦርነት መሰል የተኩስ ልውውጥ 17 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጋምቤላን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በተወሰዱ እርምጃዎች ላይማጣራት እንዲያደረግ ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል በነቀምቴ ከተማ ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ ወጣት በጸጥታ ኃይሎች መገደሉን ከሟች ቤተሰቦች መካከል ገልጸዋል።
በዚህ ዙርያ ከከተማውም ሆነ ኦሮምያ ክልል ባለሥልጣናት ለማጣራት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/