በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦፌኮ መግለጫና የአብን ተቃውሞ


የኦፌኮ መግለጫና የአብን ተቃውሞ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:44 0:00

ኦፌኮ፣ ከአማራ ክልል የተነሱ ያላቸው ታጣቂዎች በተለያዩ ስፍራዎች የኦሮሚያ ክልልን ወሰን ጥሰው የመሬት ወረራ ላይ ተሰማርተዋል ሲል፤ አብን በበኩሉ የኦፌኮን መግለጫ በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ እና ግጭት ቀስቃሽ ሲል ተቃውሟል። ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና፣ ከአማራ ክልል የተነሱ ያሏቸው ታጣቂዎች በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ መልካሙ ሹምዬ በሰጡን አስተያየት ደግሞ፣ የኦፌኮ መግለጫ ኦነግ ሸኔ ያሉት አካል በኦሮሚያና በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ለሚፈፅመው ጥቃት አማራን ተጠያቂ የሚያደርግ እና በአማራ እና በኦረሮሞ ህዝብ መካከል ግጭት የሚፈጥር ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG