ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
መጠሪያው ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ስም ጋር ተያይዞ “ኦባማኬር” እየተባለ የሚታወቀው “ለአቅም ተመጣጣኝ የሆነ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅርቦት ሕግ” ዋሽንግተን ዲ.ሲ. ላይ ዛሬ ልክ እኩለ-ሌሊት ሲሆን ሙሉ በሙሉ ወደተግባር ይገባል፡፡
በዚህ ህግ መሠረትም ከአርባ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የጤና አገልግሎት ዋስትና ያልነበራቸው አሜሪካዊያን አገልግሎቱን ለማግኘት መመዝገብ ይጀምራሉ፡፡ የምዝገባው ሥራ በስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡
በዚህ የጤና አገልግሎት አቅርቦት ሕግ ላይ ግን በሪፐብሊካን እና በዴሞክራቲክ ፓርቲው እንደራሴዎች መካከል የበረታ የፖለቲካ ትንቅንቅ አይሎ ሰንብቷል፡፡
በዚህም ምክንያት የኦባማኬርን አፈፃፀም ያቀፈውን የመጭውን የአውሮፓ ዓመት /የ2014/ በጀት ማፅደቅ ሂደት በሪፐብሊካን አብላጫ መቀመጫ በተያዘው በሕግ መምሪያውና በዴሞክራቶች አብላጫ ድምፅ በሚመራው የሕግ መወሰኛ መካከል ኦባማኬርን በበጀቱ ቢጋር ውስጥ በማቀፍ እና ቆርጦ በማስወጣት ሃሣቦች የየራሳቸውን ሕግ በማመላለስ አዙሪት ውስጥ ቆይተዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በጀት የመጨረሻ ዕለት ዛሬ መስከረም ሃያ 2005 ዓ.ም ሲሆን ልክ እኩለሌሊት ላይ የበጀት ዓመቱ ያበቃል፡፡ በዚህም ምክንያት ርካሽ የጤና ጥበቃ አገልግሎት አቅርቦት ሕጉን የያዘው የበጀት ማዕቀፍ እስከዛሬ እኩለሌሊት ባለው ጊዜ በሁለቱም ምክር ቤቶች ስምምነት ላይ ተደርሶበት ካልፀደቀ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ብዙ የሥራ ክፍሎች እኩለሌሊት ላይ ይዘጋሉ፤ እጅግ አስፈላጊ ናቸው በሚባሉ የሥራ ክፍሎች ላይ ካሉ ሠራተኞች በስተቀር ስምንት መቶ ሺህ የሚሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ያለ ደመወዝ እረፍት ላይ እንዲቆዩ ይደረጋሉ፡፡
ለመሆኑ ይህ ሁሉ ትግል በዙሪያው ነግሦ ላለፉት ከሦስት ዓመታት ለዘለቀ ጊዜ የቆየው ኦባማ ኬር ምንድነው?
በዋሽንግተን ዲ.ሲ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ፋርማኮሎጂ ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የመድኃኒት መረጃ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ብሥራት ኃይለመስቀል ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡
ለዝርዝሩ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
ለአቅም ተመጣጣኝ ወደሆነው የጤና ጥበቃ አገልግሎት ዋስትና ዌብሣይት (ኸልዝኬር ዳት ጂኦቪ - www.healthcare.gov)ለመግባት፣ የአሁን መረጃ ለማግኘት ወይም ኢንሹራንስ ለመግዛት ከታች የተመለከተውን ማገናኛ /ሊንክ/ ይጫኑና ይከተሉ፡፡
https://www.healthcare.gov/
ስለ ኦባማኬር ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከታች የተመለከተውን ማገናኛ /ሊንክ/ ይጫኑና ይከተሉ፡፡
http://obamacarefacts.com/obamacare-facts.php