አዲስ አበባ —
የፕሬዚደንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኚት ለሁለቱ አገሮች ወዳጅነት አዲስ ምእራፍ ይከፍታል ተባለ።
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን በመጎብኘት የመጀመሪያው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሰለሚሆኑ ጉብኝቱ ታሪካዊ እንደሚሆን ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
ኢትዮጵያ የአፍሪቃ ሕብረት ዋና ማእከል በመሆንዋም የድርጅቱ መሪዎችና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጉብኝቱ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማዳበር እንደሚችል ይናገራሉ።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ የፕሬዚደንቱን ጉብኝት በጣም ከፍተኛና ጠቃሚ ሲሉ ገልጸው ለአንድ ምእት ዓመት ያህል በመግባባትና በትብብር የሰሩ አገሮቻችን መካከል አዲስ ምእራፍ ይከፍታል ብለዋል።
የአፍሪቃ ህብረት ምክትልና ረዳት ኮሚሽነር ኤራስቱስ ምዌንቻም ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በድርጅቱ ዋና ጽህፈት ቤት በሚጎበኙበት ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ እና የሕብረቱ ባለስልጣናት ካሁን በፊት በልዩ ልዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ የጀመሩትን ውይይት ከፍ ባለ ደረጃና በሰፊው ለመቀጠል ያስችላል ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ