ፕረዚዳንት ኦባማ የሀገሪቱ ፖሊሶች የህዝቡን ድህንነት ለመጠበቅ በታታሪነት የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸው አሞግሰዋቸዋል። ይሁንና በሌሎች ላይ የተዛቡ አመለካከቶች እንዳሉ ግልጽ ነው ብለዋል።
ኦባማ ሀዘነተኞችን ያጽናኑት በትላንቱ የቀብር ስነ-ስርአት ላይ ብቻ ሳይሆን ባለፈው ወር በአርላዶ ፍሎሪድ፣ ባለፈው አመት በቻርልስተን ደቡብ ካሮላይና እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች ሀዘንተኞችን ያጽናኑበት ሁኔታዎች ነበሩ።
“በአለም ስላለው ሁኔታ የሚኖረንን አመለካከት መቆጣጠር እንችላለን። በእርስ በራስቸን ላይ ያለውን አያያዝንም መቆጣጠር እንችላለን።”
የቀድሞው ፕረዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ባደረጉት ንግግርም የሰዎችን መልካም ገጽታ ለማሳየት ሞክረዋል።
“በህልማችን የምናየው አይነት ሰብአዊነት የተላበሰች ሀገር ለመገንባት የምንችለው መለዮ የለበሱ ወንዶችና ሴቶች በዘብ ሲቆሙ እንደሆነ እናውቀለን።”
የትላንቱ የቀብር ስነ-ስርአት በተፈጸመበት የሙዚቃ አደራሽ ውጭ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ የፕረዚዳንት ኦባማን በቀብር ስነስርአቱ መገኘት አሞግሰዋል።
በስነስርአቱ የተገኙ ቶኒ ኢቫንስ የተባሉ ካህን አፍሪቃዊ አሜሪካዊ ግን ባለፈው የሀገሪቱ ታሪክና በተፈጸሙት ተገባሮች ምክንያት ቁስሉ በቀላሉ ላይድን ይችላል። እንዳውም ነገሮች በፍጥነት ሊፈነዱ ይችላል ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።