በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሥራ ፈጠራ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የአየር ንብረት ለውጥ - መጭው የአሜሪካ አጀንዳ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በድጋሚ ከተመረጡ ወዲህም ሆነ ላለፉት ስምንት ወራት የመጀመሪያ የሆነ ሰፊ ጋዜጣዊ መግለጫ ትናንት በዋይት ኃውስ ለተገኙ ጋዜጠኞች ሰጥተዋል፡፡


በመግለጫው ወቅት ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል አንዱ የተፈጥሮ አካባቢንና የአየር ንብረት ለውጥን የሚመለከት ነበር፡፡

ሁሉንም የአየር ጠባይ ክስተት የአየር ንብረት ለውጥ ውጤት ነው ብሎ መደምደም እንደማይቻል የጠቆሙት ሚስተር ኦባማ የዓለም ሙቀት መጠን ግን እየጨመረ የመሄዱ ጉዳይና ይህም የሰው ልጅ አድራጎቶች ውጤት ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

በሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸውም ዋናው አጀንዳቸው ሥራ ፈጠራና የኢኮኖሚ ዕድገት መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አመልክተው ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይም በመጭዎቹ ሣምንታትና ወራትም ሰፊ ትኩረት እንደሚሰጡ ገልፀዋል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG