ፕሮስቴት በወንዶች መራቢያ አካላት የሚገኝ እጢ ሲሆን የወንድ የዘር ፍሬን ለማምረት የሚረዱ የሰውነት ግብዓቶችን የሚያመርት ነው። የአሜሪካ የካንሰር ማኅበረሰብ የፕሮስቴት ካንሰር በዚህ እጢ ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት ከቁጥጥር ውጪ ሲያድጉና ሲባዙ እንደሚከሰቱ ይጠቁማሉ። አንዳንድ የፕሮስቴት ካንሰሮች በፍጥነት ቢራቡም ብዙዎቹ ግን የእድገት ፍጥነታቸው ዝግ ያለ ነው።
የአለም የካንሰር የምርመር ማዕከል ባደረገው ጥናት መሰረት እ.ኤ.አ በ2020 ምርመራ ከተደረገላቸው 1.4 ሚሊየን ሰዎች ውስጥ 375 ሺ የሚሆኑና በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ይህ የካንሰር ዓይነት በወንዶች ላይ ጎልተው ከሚታዩ የካንሰር ዓይነቶች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በገዳይነቱ ደግሞ አምስተኛ ደረጃን ይይዛል። ፕሮስቴት ካንሰር በአብዛኛው እድሜያቸው ከ50 ባለፉ ወንዶች ላይ ይከሰታል። በበሽታው ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነም በሽታው በአለም ላይ በጥቁር ወንዶች ላይ በብዛት ይከሰታል።
ለመሆኑ ፕሮስቴት ካንሰርን እንዴት ማወቅ ይቻላል? ህክምናውስ ምን ይመስላል?
/ዝርዝሩን ከተያያዘው የኑሮ በጤንነት መሰናዶ ይከታተሉ/