በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወራ ጃርሶ ወረዳ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ግጭትና የተኩስ ልውውጥ ምክኒያት፣ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን የተጎጂ ቤተሰብ እና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
የተጎጂ ቤተሰብ አባል መኾናቸውን የገለጹ ግለሰብ ፣ ከቤታቸው ደጃፋ በሚገኝ ዛፍ ጥላ ስር ኾነው ቡና በመጠጣት ላይ የነበሩ ሰዎች እና ሕፃናት ጭምር ከርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ፍንጣሪ መገደላቸውን ተናግረዋል።
Embed
share
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available
ቀጥተኛ መገናኛ
በወረዳው ደረሰ በተባለው ጉዳት ዙሪያ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጀምሮ እስከ ወረዳው ድረስ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር የአሜሪካ ድምፅ ያደረገው ጥረት ባለ ሥልጣናቱ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም