ሰሜን ኮሪያ በአራት ዓመት ውስጥ ለሙከራ ከተኮሰቻቸው ሚሳዬሎች ውስጥ ትልቁን ሙከራ ማካሄዷ ተሰምቷል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ በሰጠችው መግለጫም ዋሳንግ 12 የተባለው የመካከለኛ ረጅም ርቀት ባለስቲክ ሚሳዬል መሞከሯን ገልጻለች፡፡ ይህ እኤአ ከ2017 በኋላ የመጀመሪዋ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የቅርብ ጊዜ ሙከራዋ ሚሳዬሎቹ በሌሎች አገሮች አናት ላይ ሳይበር ሊሄድ የሚችልበትን መንገድ በመቀየስ እንደሆነም አስታውቃለች፡፡
የጃፓን መንግሥት ካቢኔ ዋና ጸሀፊና ቃል አቀባይ ሂሮካዙ ማትሱኖ እንዲህ ሲሉ ተቃውመዋል
“እንደዚህ ያሉ ከበባድ የባለስቲክ ሙሳዬል ሙከራዎች የጸጥታ ምክር ቤቱን አብይ መርሆዎች የጣሱ ናቸው፡፡ አገራችን ቤጂኒግ ባለው ኤምባሲ በኩል የሰሜን ኮሪያን ድርጊት በጥብቅ ተቃውማለች፡፡”
በጥር ወር ውስጥ ብቻ 11 ሚሳዬሎችን በመሞከር ትልቁን ቁጥር ያስመዘገበችው ሰሜን ኮሪያ ይህን የምታደርገው በዩናይትድ ስቴትስና ተባባሪዎችዋ ላይ የድርድር ጫና ለመፍጠር መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ይሁን እንጂ አገሮች አገሮች ብዙም ቁብ ያልሰጡት በመሆኑ ያሰበቸውን ትልቅ ተጽእኖ አለመፍጠሯን ተንታኞች ተናግረዋል፡፡
ከለንደን ኪንግ ኮሌጅ ፕሮፌሰር ራሞን ፓቺቾ ፓርዶ እንዲህ ይላሉ
“ሰሜን ኮሪያ የሁሉንም ትኩረት ማግኘት ብትፈልግ የኒዪከለር ሙከራ ታደርጋለች፡፡ እስካሁን ያንን አላደረገችም፡፡ይሁን እንጂ ባሁን ሰዓት በኮሪያ ሰርጥ የሚሆነውን በቅርብ ከሚከታተሉት በቀር ማንም አስተያየቱ እየሰጠ አይደለም፡፡”
የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በቅርቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ሌላ ትልቅ ሙከራ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይሁን እንጂ ባለሥልጣናቱ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ለድርድሩ ክፍት በሯ ክፍት ቢሆንም በፕሬዚዳንት ደረጃ የሚደረግ ግንኙነትን ግን አትፈልገውም ሲሉ መናገራቸውም ተመልክቷል፡፡