በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለምቀፍ የኒውክሊየር መሳሪያዎች አስወጋጅ ዘመቻ የኖቤል የሰላም ሽልማት


Sascha Hach, right, and Xanthe Hall of the International Campaign to Abolish Nuclear Weapons ICAN Germany, pose in their office in Berlin, Oct. 6, 2017.
Sascha Hach, right, and Xanthe Hall of the International Campaign to Abolish Nuclear Weapons ICAN Germany, pose in their office in Berlin, Oct. 6, 2017.

ዓለም ቀፍ የኒውክሊየር መሳሪያዎች አስወጋጅ ዘመቻ (ICAN) የዘንድሮ እኤአ 2017 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸለመ።

ዓለምቀፍ የኒውክሊየር መሳሪያዎች አስወጋጅ ዘመቻ (ICAN) የዘንድሮ እኤአ 2017የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸለመ።

የኖርዊዩ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ መሪ በሪቲ ረኢስ አንደርሰን ሽልማቱን ይፋ ሲያደርጉ ባሰሙት ንግግር

“ባሁኑ ወቅት ዓለማችን ለረጅም ጊዜ ከነበረው የከፋ ደረጃ ኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ሥራ ላይ የመዋል አደጋ ተደቅኖባታል” ብለዋል።

የኖቤል የሰላም ሽልማቱ ለኒውክሊየር መሳሪያ አስወጋጅ ዘመቻው የመሰጠቱ ዜና የተሰማው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ኢራንና ሰሜን ኮርያን ከኒውክሊየር ዓቅማቸው በተያያዘ “ወዮላችሁ” እያሉ በሚገኝበት ባሁኑ ወቅት ነው።

ከኢራን ጋር የተደረሰውን ውል

“ከማናቸውም የከፋ ውል” ሲሉ የጠሩት ፕሬዚደንት ትረምፕ ውሉን እሰርዛለሁ ብለው እየዛቱ ናቸው።

በቅርቡ በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር

ሰሜን ኮሪያን ደግሞ ድምጥማጧን እንድናጠፋ ሳንገደድ እንቀርም ማለታቸው ይታወሳል።

የዘንድሮን የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚው /ICAN/ ፌስቡክ ላይ ባወጣው መግለጫ እየተካሄደ ያለው የተጧጧፈ እሰጥ አገባ እጅግ ዘግናኝ ወደሆነ አቅጣጫ ሊያመራ እንደሚችል አመልክቶ፣ የኒውክሊየር ግጭት ዳግሞ ገዝፎ እያንዣበበ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሀገሮች ያለምንም ማወላወል የኒውክሊየር መሳሪያ እንደሚቃወሙ ማሳወቅ ይገባቸዋል ሲል አሳስቡዋል።

የኖቤል ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ /ICAN/ የሰላም ሽልማቱ የተሰጠው ኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ሥራ ላይ ቢውል ስለሚያከትለው ሰብዓዊ መዘዝ ትኩረት ለመሳብ እና መሳሪያዎቹን የሚያግድ ውል ላይ እንዲደረስ ባካሂደው ጥረት መሆኑን ገልጿል።

የኖቤል ተሸላሚው ድርጅት የተባበሩት መንግሥታት የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ዕገዳ ውል እንዲከበር ጥረት የሚያደርጉ በአንድ መቶ ሃገሮች የሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ጥምረት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG